በዕጅ የሚዘወር ማስተላለፊያ በመካከለኛው ምስራቅ በንግድ ተሸከርካሪዎች ላይ የተለመደ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት አምራቾች የትኩረት አቅጣጫቸውን ራስ ሰር/አውቶሜትድ ወደሆኑ የማርሽ ሳጥኖች በማዞር ላይ ይገኛሉ እንዲሁም ኢንዱስትሪው ጥሩ ጎናቸውን መመልከት ጀምሯል፡፡
ከዚህ እያደገ ከመጣው ሁኔታ ጋራ በተጓዳኝ ኢቬኮ በቅርቡ በዱባይ አውቶድሮም በሞተር ከተማ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አከፋፋይ ከሆነው ከሰዒድ መሐመድ አል ጋንዲ እና ልጆቹ (ኤስኤምኤጂ) ጋራ በመተባባር በተከፈተው ትእይነት ላይ ትራከር ዩሮትሮኒክን ይፋ አድርጓል፡፡ ከመላው ኢሜሬትስ የከተማ አስተዳደሮችን፣ የግንባታ ድርጅቶችን፣ የድንጋይ ካባዎችን፣ የትራንስፖርት ድርጅቶችን፣ እና ሌሎች ድርጅቶችን በመወከል ከ150 በበለጡ ደንበኞች ተጎብኝቷል፡፡
የትራከር ልዩ ልዩ መልኮች ተመርጠው ለዕይታ የቀረቡበት እና የትዕይንቱ ኮከብ ትራከር ዩሮቶኒክ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ገፅታዎች ማለትም ከገልባጭ፣ መጠቅጠቂያ/ኮምፓክተር፣ የውሃ ጋንና ማደባለቂያ/ሚክሰር በመሆን ከአራት ትራከር ኤዲ380 ሞዴሎች ጋራ በመሆን ቀርቧል፡፡ ተሳታፊዎች ትራከሩን በመንገድ ላይ መሞከር እንዲሁም የተሽከርካሪውን አፈጻጸም በራሳቸው ለመሞከር ዕድሉ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከትራከሩ ባሻገር በኢቬኮ መስመር ሌሎች ተሽከርካሪዎች በትእይንቱ ላይ ዩሮካርጎን እና ኒው ዴይሊን ጨምሮ ቀርበዋል፡፡
የአውቶሜትድ ማርሽ ሳጥን መተዋወቅ ገበያው ምቾትን እና ጠቅላላ የባለቤትነት ወጪዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት እያደገ ባለበት ጊዜ ዕውን መሆኑን በአል ጋንዲ አውቶ ውስጥ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ግርሃም ተርነር ያብራራሉ፡፡ እርሳቸው አውቶሜትድ የሆነው የማርሽ ሳጥን የሚቀለው ለአሽከርካሪዎች ብቻ ሳይሆን ያነሰ ጥገና መፈለጉንና ያነሰ የፍሪሲዮን እርጅና እንዳለው በመጠቆም “በአሁኑ ወቅት እያወራን ያለነው ይበልጥ ወጪ ቆጣቢ ስለሆነው ትራክተር ነው፡፡” ይላሉ፡፡
ተርነር እንደሚናገሩት በንግድ ተሽከርካሪዎች ረገድ የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ባጠቃላይ የመንገድ ደህንነት ደረጃ ማሳደግን ዕውን ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡ “በሙከራ መድረኮች፣ በደህንነት ፕሮግራሞች ወዘተ.. ላይ በርካታ የመንግስት መነሳሳት መኖሩን ሁላችንም ለመመልከት ችለናል ስለዚህ ወደፊት ኢንቨስት የማድረግ ዕድሉ እዚህ የተገኙ የሁሉም ማኀበራት ይሆናል፡፡”
በኢቬኮ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የቢዝነስ ዳይሬክተር የሆኑት ሉካ ስራ እንደተናገሩት በኢኤምኢኤ ክልል ወደአውቶሜትድ ማርሽ ሳጥኖች የሚደረገው ለውጥ የጀመረው ከ10-15 ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ‹‹ወደ ደቡባዊ አውሮፓ ሐገራት የተስፋፉት እና አሁን እዚህ በመምጣት ላይ ባሉት ዩኬን፣ ጀርመንን፣ ፈረንሳይን በመሳሰሉ ሰሜናዊ አውሮፓ ሀገራት በመሰረቱ የሚንቀሳቀስ ነበረ፡፡››
“የባለቤትነት ጠቅላላ ወጪ፣ የተሸከርካሪ ቆይታ፣ እንዲሁም በማሽከርከር ሂደቱ ላይ መጥፎ የማሽከርከር አካሄድ ያለው ተፅዕኖ፣ የፍሬን ስርዐት እና የነዳጅ ፍጆታ ይበልጥ ተወዳጅ እየሆኑ የመጡ ፅንሰ ሐሳቦች ናቸው፡፡”
እርሳቸው እንደተናገሩት ስለዚህ አዲሱ ትራከር ዩሮቶኒክ በክልሉ እና በተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች የሚገኙ ማናቸውንም የኢቬኮ ደንበኞች በአወንታዊ መንገድ የሚጠቅም ነው፡፡
የዩሮቶኒክ ማርሽ ሳጥን በመተዋወቁ የትራከር ልዩነት ከተለመደው የሰፋ ሲሆን እና ከርሰር 13 ሞተሮችን እና ሁለት ጋቢናዎችን (ሀይ-ላንድ እና ሀይ-ትራክ) ያካተተ ነው፡፡ ወጥ ከባድ ተሽከርከሪ ምርቶች በ4 X 2፣ 4 X 4፣ 6 X 4፣ 6 X 6፣ 8 X 4 እና 8 X 8 ገፅታዎች ውስጥ ከ380ኤችፒ እስከ 440ኤችፒ የሐይል ምጣኔ ጋር ይገኛሉ፡፡ ትራከር ከባድ ተሽከርከሪ ምርቶች በ4 X 2፣ 4 X 4፣ 6 X 4 እና 6 X 6 ገፅታዎች ውስጥ ከ380ኤችፒ እስከ 440ኤችፒ የሐይል ምጣኔ ጋር ይገኛሉ፡፡
የዩሮቶኒክ አውቶሜትድ የማርሽ ሳጥን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል አውቶማቲክ በሆነ ሞዴል ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ አውቶማቲክ ማርሽ ማስነሻ እና ማቀዝቀዣ በጭነት ሁኔታዎች፣ በመንገድ ሁኔታዎች እና በማሽከርከር ዘይቤ፣ የተሽከርካሪውን አቅም ከፍ ለማድረግ፣ የነዳጅ ፍጆታን እና ምቾትን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማድረግ በሚል ስሌት የሚደረግበት ይሆናል፡፡
በስብቀት ሀይል ከሚደረግ የማዋደድ ስራ ይልቅ በእጅጉ ፈጣን በሆነ የሞተር ፍጥነትን በኤሌክትሮኒክ የማስማማት ዘዴ የማርሽ ፍጥነቶች እንዲዋደዱ የሚደረግ ይሆናል፡፡ አሽከርካሪው በአስቸጋሪ ርቀት ላይ ተመሳሳይ ሬሾ ማስጠበቅ ካስፈለገ የማርሽ ለውጦችን ለመቆጣጠር በከፊል አውቶማቲክ ወደ ሆነው ሞዴል ሊቀይረው ይችላል፡፡
የዩሮቶኒክ የማርሽ ሳጥን በዜድ ኤፍ አማካኝነት ከኢቬኮ ጋር በመሆን የተዘጋጀ መሆኑን ስራ ጠቁሟል፡፡ ‹‹ተሸከርካሪዎቻችን በጣምራ ንድፍ ስትራቴጂ የተሰሩ ሲሆን እንዲሁም የተሻለ መፍትሔ ለራሳችን ለማቅረብ የተሻሉ አጋሮችን እንፈልጋለን፡፡ ለዚህ ነው ዜድኤፍ የተመረጠው፡፡ ይኸውም ከፍተኛ የአርት ቴክኒክን የሚጠቀሙ እንዲሁም አቅራቢ የሆነ ድርጅት ነው፡፡››