የመጠየቂያ ቅጽ
ድፍንና ጉልበት ያለው
ክላይማ ሲደብልዩኤስ ሞጁል ከ 60 ጫማ እስከ 50 ሜትር እና ከዛ በላይ ለሆኑ መርከቦች አይነተኛ መፍትሄ ነው፡፡ ከማይዝግ ብረት ፍሬን የተሰራ ማቀፊያ ማደንደኛዎች/ኮንዴንሰሮችና ማኒፎልዶችን ለባህር ውሃና ክላይማ ሲደብልዩኤስ ፈሳሽ የማያስተላልፍ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል ንፁህ ውሃ የሚሽከረከርበት በውስጡ የተገነባ ሞጁላር ሲስተም አለው፡፡
ብቁና አስተማማኝ
በልዩ ሁኔታ የተሰራው የክላይማ ማይክሮ ፕሮሰሰር በሲደብልዩኤስ መቆጣጠሪያ ሳጥን፣ መመልከቻ ውስጥ የሞድ ባስ አገናኝ ፕሮቶኮልን በመጠቀም የሲስተሙን አሰራርና አስተማማኝነት ከፍ ለማድረግ ሁሉንም ወሳኝ የሲተሙን መለኪያዎች በሙላ ይቆጣጠራል፡፡ ሁሉም ሲደብልዩኤስ ሶሎዎች በቀያሪ ማጫወቻዎች ላይ ይገኛሉ፡፡ የክላይማ የተለየ የቀዘቀዘ ውሃ ቀያሪዎች የመጀመሪያውን ሙሉ በሙሉ ያስወግዱና የሲደብልዩኤስ አካሎች የሀይል ፍጆታ እስከ 30% ድረስ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
በከፍተኛ ጥራት ስለመሰራቱ
የባህር ውሃ አደንዳኝ/ኮንዴንሰር እና ከዛ ጋር የተያያዘ የባህር ውሃ ሰርኪዩት ወይም ማኒፎልዶች በባህር ውሃ እንዳይገባባቸው ተደርጎ በባህር ደረጃ የተሰሩ ናቸው፡፡ የንፁህ ውሃ መተላለፊያ መስመር በመዳብና በማይዝግ ብረት የተሰራ ሲሆን አማቂው በፀረ ንዝረት ላይ ይገጠማል፡፡
የሞጁላር ንድፍ ማለት ክላይማ እጅግ አስተማማኝ በሆነ ንድፍ የተሰራ መሆኑን የሚሳይ ነው፡፡ እያንዳንዱ አማቂ እራሱን የቻለ ሲሆን፣ አስፈላጊ ከሆነ፣ ከሲስተሙ ጋር መተላለፍና ሌላው ሲስተም በትክክል እንዲሰራ ተደርጎ እና በመርከቡ ላይ ያለው ምቾት በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ ሌላውን ሲስተም ትቶ ከዛ ውስጥ ሊወጣ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተጨማሪ ሞጁሎች ለሁሉም ሲስተም ከፍተኛ የሆነ የማቀዝቀዝ አቅም ለመስጠት ተጨማሪ ሞጁሎች ሊጨመሩ ይችላሉ፡፡
ሁሉም የኤሌክትሪክ ግንኙነቶች ተሰርተዋል፣ ሳይጨረሱ የቀሩትም በመጨረሳ ገጠማ ግዜ የሚሰሩ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ሞጁል እንዲሁም አጠቃላዩ ሲስተም ከፍተኛ ጥራት ባለው የመቆጣጠሪያ መስፈርት መሰረት የሙከራ ሂደት እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡
ዝርዝር መግለጫው እንዲመጥን ተደርጎ የተሰራው
ከ 72.000 እስከ 576.000 ቢቲዩ/ኤ ድረስ የሪቨርስ ሳይክል ወይም የማቀዝቀዣ ብቻ አማራጮች ያሉት ሲሆን የሞጁላሩ ንድፍ እያንዳንዱ የሲደብልዩኤስ ሲስተም ከትንሹ ቦታ ላይ ከፍተኛ ቢቲዩ/ኤች በመስጠት ለመርከቡ መጠን እንዲበቃ ተደርጎ መሰራቱን ያረጋግጣል፡፡
ፍሬሞቹ እንደተፈለገው መደርደሪያዎችን/ራኮችን በመፍጠር መገጣጠም የሚችሉ ሲሆን የባህር ውሃ መተላለፊያ አቅጣጫን መቀየርም ይቻላል፡፡ ፍሬሞቹ በሞተር ክፍል ውስጥ ወይም በማሽኑ ቦታ ያሉ ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር እንዲመሳሰሉ መቀባት የሚሉ ሲሆን ይህም ሲስተሙ በጥሩ ሁኔታ እንደሚሰራ የሚያረጋግጡና ፍሬሞቹ ኤሌክትሪክ በማያስተላልፉ ክፍሎች ሊሸፈኑ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የሲደብልዩኤስ ሞጁል ስርአት ያለ ፍሬም ሊገጠም ይችላል፡፡